Oduu Oduu

ነሐሴ 10 ቀን 2013 ዓ.ም.

ዛሬ በየተቋሞቻችን ግድግዳዎች ላይ ቅንነት፣ ታማኝነት፣ ሕግን ማክበር፣ ሚስጥር መጠበቅ፣ ሀቀኝነት፣ ተጠያቂነት፣ የህዝብን ጥቅም ማስቀደም ወዘተ የሚሉ መርሆዎች በወርቃማ ጽሁፍ ተከሽነውና ተለጠፈው ይገኛሉ፡፡ አብዛኛዎቹ ሰራተኞችም እነዚህን ወርቃማ መርሆዎችን ያውቃሉ ተብሎ ይገመታል፡፡

ይሁን እንጅ ተግባራዊነቱ ላይ ሁሉም ዘንድ ክፍተቶች እንዳሉ ግልፅ ነው፡፡ ታዲያ እነዚህን ወርቃማ መርሆዎች ዛሬ ላይ ትኩረት ሰጥተን በተሰማራንበት የሥራ መስክ ሁሉ ተግባራዊ ካላደረግን ትውልዱ ከእኛ ምን ይማር ይሆን? ተቋማዊ የሥነምግባር እሴቶችን በመገንባት ረገድስ ኃላፊነታችንን እንዴት እየተወጣን ነው? ሁላችንም እራሳችንን እንጠይቅ?