ስልጣንና ተግባራት ስልጣንና ተግባራት

ፌደራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና  ኮሚሽን መቋቋም አስፈላጊነት፣ ሥልጣን፣ ተግባርና ኃላፊነቶች እንዲሁም የኮሚሽን መስሪያ ቤቱ ተጠሪ ተቋማት

 

መግቢያ

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የፌደራል መንግስት ሕገ መንግስታዊ ሥልጣንና ኃላፊነቱን በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችለው አወቃቀር አስፈላጊ በመሆኑ፣ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ ውጤታማ፣ ዘላቂ እና ተቋማዊ ለማድረግ፤ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን የአደረጃጀት፣ ሥልጣንና ተግባር እንደገና መወሰን አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

 

  1. የፌደራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና  ኮሚሽን መቋቋም አስፈላጊነት

ሀገራዊ የሙስናና ብልሹ አሠራሮችን ተቋማዊ በሆነ አደረጃጀት የመዋጋትና የመከላከሉን ስራ በባለቤትነት የሚያስተባብር ተቋም በፌደራል ደረጃ ማደራጀት በመሆኑ የፌደራል የሥነ  ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽንን በአዋጅ ቁጥር 235/1993/2000 ግንቦት 16 ቀን 1993 ዓ.ም እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡

 

  1. የፌደራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና  ኮሚሽን ተግባራትና ኃላፊነቶች

በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጸደቀው አዋጅ ቁጥር 433/1997 አንቀጽ 883 ንዑስ አንቀጽ ---- መሰረት ኮሚሽን መስሪያ ቤቱ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ተሰጥተውታል፡፡

  • የኮሚሽኑን የበላይ አመራር እና ዳይሬክተሮችን በህግ ጉዳይ ማማከር፣
  • የኮሚሽኑ ህገ ደንብ፣ መመሪያና ማኑዋሎች ከተልዕኮው አንፃር በመቃኘት ማወጣት፣
  • የሀገሪቱን የፀረ ሙስና ህጎች መከበራቸውን መከታተልና ማማከር፣
  • ሀገሪቱ ተቀብላ ያፀደቀቻቸው የፀረ ሙስና ትግል ኮንቬንሽኖችን ማስተግበር፣
  • በሀገር ህግና ፖሊሲ መሰረት ዓለም ዓቀፍ ትብብርን ማስፈፀም፣
  • ኮሚሽኑ የሚያደርጋቸውን ውሎችና የሚገባቸውን ግዴታዎች ህጋዊ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣
  • ለኮሚሽኑ የሥራ ክፍሎች የውል ሰነዶችን ማዘጋጀት፣
  • ክፍተት ያለባቸውንና በስራ ላይ ያሉ ኮሚሽኑ የሚገለልባቸውን ህጎች በማጥናት እንዲሻሻሉ በጥናት የተደገፈ የውሳኔ ኃሳብ ማቅረብ፣
  • ኮሚሽኑ በሚከሰስበትም ይሁን ክስ በሚመሰርትባቸው ጉዳዮች ኮሚሽኑን በመወከል በፍርድ ቤትና መሰል ተቋማት በመቅረብ  ውሳኔ አስኪያገኙ ድረስ ተገቢውን የህግ ክርክር ማድረግ፣ በስራ ላይ መዋላቸውን ማረጋገጥ፣
  • በኮሚሽኑ በተዘጋጁ ህጎች፣ደንቦች፣መመሪያዎች/ማኑዋሎች እና አስፈላጊ ናቸው በተባሉ ሌሎች ህጎች  ላይ ለኮሚሽኑ አመራርና ሠራተኞች ግንዛቤ መፍጠር፣
  • የፀረ ሙስና ህጎች አፈፃፀምን መከታተል፣ውጤታማነታቸውን ማረጋገጥ፣
  • በጸረ ሙስና ትግል ዙሪያ ከህብረተሰቡ ለሚቀርቡ የምክር አገልግሎት ጥያቄዎች የምክር አገልግሎት መስጠት፣
  • ኢትዮጵያ ተቀብላ ያፀደቀቻቸው አለምአቀፍና አህጉር አቀፍ የፀረ ሙስና ኮንቬንሽኖችን ትግበራና ግንኙነቶችን ማስፈፀም፣
  • የፀረ ሙስና ኮንቬንሽኖች አተገባበር ላይ ተቋማት ውስጥ የተሻለ አፈፃፀምና ልምድ ካላቸው ተቋማት ተሞክሮዎችን በመውሰድ መቀመርና ማስፋፋት፣
  • አህጉር አቀፍና አለም አቀፍ ፀረ ሙስና ኮንቬንሽን ፈራሚ ሀገራት የጋራ ጉባኤ እንዲሁም ሌሎች አህጉርና አለምአቀፍ የፀረ ሙስና እንቅስቃሴ ዙሪያ ስብሰባዎች ኢትዮጵያ እንድታዘጋጅ የመነሻ ኃሳብ ማቅረብ፣
  • ሌሎች ተዛማጅ ስራዎችን ማከናወን፡፡
  1. ኮሚሽን መስሪያ ቤቱ ተጠሪ ተቋማትን በተመለከተ

በአዋጅ ቁጥር ------ አንቀጽ ---መሰረት የሚከተሉት አስፈጻሚ አካላት ተጠሪነታቸው ለ ፌደራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና  ኮሚሽን ተደርጓል፡፡

1.የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣

2.የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሀግ፣

3.የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣

4.የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣

5.የፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከል፣

6.የፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከል፣

7.የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት፣

8.የፌደራል ዋና ኦዲተር

ናቸው፡፡