ኮሚሽኑ በ2013 በጀት ዓመት ሙስናን ለመከላከል በተሰራው ሥራ በክልሉ ያለ አግባብ ሊወጣ የነበረ ከ3 ሚሊዮን 5 መቶ ሺህ በላይ ብር የመንግስት ሀብት ወደ መንግስት እንዲመለስ መደረጉን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ክቡር አቶ ካሊድ ኑሬ ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽነሩ እንደገለፁት በክልሉ የሚገኙ የህዝብ ተመራጮች፣ የመንግስት ተሿሚዎችና ሰራተኞችን ሀብትና ንብረታቸውን የማስመዝገብ፣ ዝርዝር መረጃዎችን የመሰበሰብና የማደራጀት ስራ ተከናውኗል፡፡

በክልሉ በሚገኙ 41 ተቋማት ውስጥ የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎችን በመመደብ የዕቅዱን 70 በመቶ ማሳካት መቻሉን እና ለዚህ ውጤት መገኘት ተቋማት ድጋፍ ማድረጋቸው ተጠቁሟል።

የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ባከናወናቸው ሥራዎች በፌደራል ደረጃ ተሸላሚ የነበረ ሲሆን ለውጤቱ መሳካት የበኩላቸውን አስተዋኦ ላበረከቱ የኮሚሽኑ ሰራተኞች የማበረታቻ ሽልማት መስጠቱንም ኮሚሽኑ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ዘግቧል፡፡



No comments yet. Be the first.